Sheger FM Radio 102.1
ሸገር የእናንተ ነው!
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23 ቀን 2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ይህ ከአዲስ አበባ በ250 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ፕሮግራም እንዲያሰራጭ ፈቃድ አግኝቶ የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ሊያተርፍ ችሏል፡፡ ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡ የሸገር ዓላማ ከወገናዊነት የነፃ ትክክለኛ የሕዝብ ድምፅ መሆን፣ ሥነ ምግባርን የጠበቀ የጋዜጠኝነት መርህን መከተልና የተሣካለት የኢንፎቴይመንት (information & entertainment) ሬዲዮ ጣቢያ መሆን ነው፡፡ ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ ሸገር የእናንተ ነው! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
Listen to this radio station and thousands more from around the globe anytime, anywhere with the Streadio App.
Get the Streadio app for free
- Listen to radio stations from around the world.
- Discover stations by genre, country, or language.
- Record live radio broadcasts for later listening.
- Control playback from notifications.
- Add custom radio station stream URLs.
- ...and many more features




















